ደህንነት እና እርዳታ
የBinance እና Binance Card ማጭበርበር፦ 12 ቀይ ምልክቶች
የBinance እና Binance Card ማጭበርበርን በBinance Verify መለየት፣ 12 ቀይ ምልክቶችን ማወቅ እና የpassword፣ APK፣ seed phrase፣ KYC ወይም ክፍያ ጉዳትን መቆጣጠር።
የመጨረሻ ማረጋገጫ፦ 2026-08-25። ይህ መመሪያ የBinance ስም የሚጠቀሙ አስመሳዮችን፣ የውሸት Card ኤጀንቶችን፣ የKYC ሰነድ ስርቆትንና “ገንዘብ እናስመልሳለን” የሚል ሁለተኛ ማጭበርበርን ለመለየት ነው። የጠፋ ገንዘብ እንደሚመለስ አያረጋግጥም፣ የባንክ፣ የመድረክ፣ የሕግ አስከባሪ ወይም የብቁ ባለሙያ ሂደትንም አይተካም።
ሶስት ዋና ህጎች፦ OTP፣ የይለፍ ቃል፣ Passkey approval፣ API key፣ seed phrase፣ ሙሉ የካርድ ቁጥር ወይም CVV ለማንም አይስጡ፤ በሌላ ሰው የተላከ APK፣ browser extension ወይም remote-control app አይጫኑ፤ ለ“ማስነሳት፣ refund፣ ካርድ ማንቃት ወይም recovery” ሁለተኛ ክፍያ አይላኩ።

እውነተኛ የBinance Verify ገጽ፦ መሣሪያው የምንጭ ማንነትን ብቻ ያግዛል፤ ኢንቨስትመንት፣ listing፣ ኤጀንትነት ወይም የገንዘብ ጥያቄ እንደተፈቀደ አያረጋግጥም። በስክሪንሾቱ ምንም የግል መረጃ አልገባም።
በ60 ሰከንድ የሚደረግ ማረጋገጫ
- መልስ መስጠትን ያቁሙ፣ የተላከልዎትንም ሊንክ አይጫኑ።
binance.comን በራስዎ ይጻፉና Binance Verifyን ይክፈቱ።- በገጹ የሚደገፈውን URL፣ email፣ phone፣ Telegram ወይም social account ይፈትሹ።
- ምንጩ verified ቢሆንም የተጠየቀውን የገንዘብ ወይም የመለያ ተግባር በተናጠል ያረጋግጡ፤ ማንነት መረጋገጥ ተግባሩ ተፈቅዷል ማለት አይደለም።
- ለመለያ ችግኝ ከኦፊሴላዊ App/website ወደ Support በራስዎ ይግቡ፤ ስክሪንዎን ለሌላ ሰው አያስተዳድሩ።
12 ቀይ ምልክቶች
- “በማንኛውም አገር Binance Card እከፍትልዎታለሁ” የሚል ዋስትና።
- የሐሰት አድራሻ፣ የሌላ ሰው ሰነድ ወይም ባንክ መለያ መጠቀም እንዲችሉ መንገር።
- OTP፣ Authenticator code፣ setup key ወይም Passkey approval መጠየቅ።
- የይለፍ ቃል፣ API secret፣ seed phrase፣ ሙሉ ካርድ ቁጥር ወይም CVV መጠየቅ።
- ያልታወቀ APK፣ browser extension፣ AnyDesk ወይም TeamViewer እንዲጫኑ መጠየቅ።
binance.comን የሚመስል ግን ፊደሉ የተለየ ዶሜይን።- “በጥቂት ደቂቃ ውስጥ ካልከፈሉ መለያው ይዘጋል” የሚል ግፊት።
- ውይይቱን ወደ የግል Telegram/WhatsApp ቻት ማዘዋወር።
- መለያን “ለመክፈት፣ refund ለማድረግ ወይም ገንዘብ ለማረጋገጥ” crypto እንዲልኩ መጠየቅ።
- የተወሰነ ትርፍ፣ ዜሮ አደጋ ወይም ጉዳት በሙሉ እንደሚመለስ ዋስትና።
- “Recovery agent” ነኝ ብሎ የመጀመሪያውን ጉዳት ለመመለስ ሌላ ክፍያ መጠየቅ።
- ቻት፣ order፣ transaction hash ወይም የባንክ ማስረጃን እንዲሰርዙ መንገር።
አንድ ምልክት ብቻ ማጭበርበርን ሁልጊዜ አያረጋግጥም። ሚስጥራዊ መረጃ፣ remote control ወይም ተጨማሪ ክፍያ ከተጠየቀ ግን ወዲያውኑ ያቁሙ።
ምን ተጎድቷል? በሁኔታው መሰረት ይስሩ
| ሁኔታ | አሁን የሚደረግ | የሚቀመጥ ማስረጃ |
|---|---|---|
| ተጠርጣሪ መልዕክት ብቻ ደርሷል፣ ሊንክ አልከፈቱም/አልከፈሉም | ውይይቱን ያቁሙ፤ Binance Verifyንና ኦፊሴላዊ Supportን ይጠቀሙ | account፣ URL፣ phone፣ ጊዜና ሙሉ ውይይት |
| የይለፍ ቃል አስገብተዋል ወይም ያልታወቀ Passkey አጽድቀዋል | ያልፈቀዱት ግብይት/ማስወጣት ካለ ከንጹህ መሣሪያ Disable Account ወይም ኦፊሴላዊ Supportን መጀመሪያ ይጠቀሙ፤ ከዚያ የBinanceና የኢሜይል የይለፍ ቃል ይቀይሩ፣ devices፣ Passkeys፣ 2FA እና API keysን ይፈትሹ | Login alerts፣ device list፣ transaction history እና support ticket |
| APK ወይም remote-control app ጭነዋል | የremote sessionንና networkን ያቋርጡ፣ በተጎዳው መሣሪያ ሌላ credential አያስገቡ፤ ከሌላ ንጹህ መሣሪያ መለያዎችን ይጠብቁ። ከዚያ በAndroid/iOS/Windows/macOS ኦፊሴላዊ መመሪያ appን ያስወግዱና security scan ያድርጉ፤ መበከሉ ካልጠፋ የመሣሪያ ማስጀመሪያ ማጽዳት/reset ከባለሙያ ጋር ያስቡ | App name፣ download URL፣ permissions እና ጊዜ |
| Seed phrase ወይም private key አጋርተዋል | ያንን wallet እንደተጎዳ ይቆጥሩ፤ ከንጹህ መሣሪያ አዲስ wallet ይፍጠሩ፣ አደጋውንና network feeን ካረጋገጡ ቀሪ ንብረትን ወደ አዲሱ ያዛውሩ፣ አጠራጣሪ token approvalsን ይሰርዙ። “Recovery agent” ለሚል ሰው seed phrase ወይም ክፍያ አይስጡ | የተጋራበት ቦታ፣ wallet address፣ transaction hash እና approvals |
| ID/KYC ሰነድ ወይም selfie ልከዋል | ሌላ ሰነድ አይላኩ፤ Binanceን ያሳውቁ፣ የአካባቢውን identity-theft/ሕጋዊ ሂደት ይጠይቁ | የተላከው ፋይል፣ ተቀባይና ውይይት፤ ሲያጋሩ ሚስጥራዊ መረጃን ይሸፍኑ |
| ያልፈቀዱት የባንክ/ካርድ ክፍያ አለ | ባንክ፣ card issuer ወይም payment providerን ወዲያውኑ ያነጋግሩ፤ Binance Supportንም ያሳውቁ | መጠን፣ ጊዜ፣ merchant፣ statement እና ticket |
| Crypto ልከዋል | Transaction hash፣ network፣ መጠንና receiver addressን ያስቀምጡ፤ ለተሳተፈው platformና ለተገቢ ባለሥልጣን ፈጥነው ሪፖርት ያድርጉ | Block explorer record፣ ቻትና የክፍያ ማስረጃ |
በblockchain ላይ የተረጋገጠ ግብይት ብዙ ጊዜ ለመመለስ አስቸጋሪ ነው። ፈጣን ሪፖርት ግን መድረክ ወይም ሕግ አስከባሪ ተያያዥ መለያዎችን እንዲለይ ሊረዳ ይችላል፤ “ገንዘቡ በእርግጥ ይመለሳል” የሚል ቃል አይታመኑ።
ለኢትዮጵያ ተጠቃሚዎች ተጨማሪ ምርመራ
- Card ወይም አገልግሎት በሌላ አገር መኖሩ በኢትዮጵያ ማመልከት ይቻላል ማለት አይደለም።
- Binance account፣ KYC ወይም በapp ውስጥ የሚታይ አዝራር የNBE ፈቃድ አይደለም።
- ብርን ከcrypto ጋር የሚያጣምር P2P ከመጀመርዎ በፊት የNBE 2026-02-27 ማስታወቂያን ያንብቡ።
- ጉዳዩ ባንክ፣ payment account፣ identity theft ወይም ተጠርጣሪ የገንዘብ ተግባርን ካካተተ NBE Contactን ይጠቀሙ፤ ገጹ 6230 እና የመልዕክት ቅጽ ይዟል። አስቸኳይ የወንጀል ወይም የግል ደህንነት አደጋ ካለ የአካባቢውን ሕግ አስከባሪ ያነጋግሩ።
ከሪፖርት በፊት ማስረጃ ያዘጋጁ
ሙሉ URL፣ social account፣ phone number፣ wallet address፣ transaction hash፣ ጊዜ፣ መጠንና platform ticket ያስቀምጡ። ስክሪንሾት ሲያጋሩ OTP፣ password፣ Cookie፣ Token፣ ሙሉ card number፣ CVV እና የማያስፈልግ የID ቁጥር እንዳይታይ ይሸፍኑ። “ማስረጃ ለመሰብሰብ” ብለው ከአጭበርባሪው ጋር ግብይቱን አይቀጥሉ።
ኦፊሴላዊ ምንጮች
- Binance Verify
- Binance Academy፦ Common Bitcoin Scams and How to Avoid Them
- Binance Academy፦ Seed Phrase ምንድን ነው?
- Binance Academy፦ Secure Your Binance Account in 7 Simple Steps
- NBE Contact
